Skip to main content

English | español | 中文 | français | Việt Nam | 한국어 | አማርኛ | Português

ዲስትሪክት አቀፍ ክልላዊ ትንተና
DISTRICTWIDE BOUNDARY ANALYSIS

 

ዲስትሪክት አቀፍ የክልል ጥናት ትንታኔ: ምዕራፍ 2 ወደ አንድ ገጽ የሚያመጣ ተሳትፎ

ያስታውሱ... ዲስትሪክት አቀፍ የማካለል ትንተና እንደገና ምን ይባላል?
የዲስትሪክት አቀፍ የድንበር ትንተና ለሞንትጐመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ወሰን ለመከለል አጠቃላይ ሁለገብ የመመዘኛ ጥናት ዳሰሳ ትንተና ለመስጠት የተዘጋጀ ነው። የትምህርት ቤት አገልግሎት አጠቃቀም፣ የት/ቤት አቅም፣ የተማሪ የብዝሃነት ስብጥር እና የትምህርት ቤቶች ቅርበትን በሚመለከት ቀዳሚው ተግባር የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከ2019 የፀደይ-ስፕሪንግ ወራት ጀምሮ በተደረገው የማሳተፍ ጥረት ላይ የተገነባ ሲሆን በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ትርጉም ያለው የተቀናጀና የብቃት ባህልን ያዳበሩ ትምህርት ቤቶችን በመፍጠር ረገድ ያሉትን ተግዳሮቶች በሚገባ ለመረዳት እንዲቻል ተከታታይ መድረኮችን በማዘጋጀት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማሳተፉን ይቀጥላል።

አሁን ማድረግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
ባለፉት 20 ዓመታት የ MCPS የተማሪዎች ምዝገባ ከ30,000 በላይ ጭማሪ አሳይቷል። ይህ እድገት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በአገር አቀፍ ደረጃ ብዝሃነት ካላቸው ከከፍተኛዎቹ ዲስትሪክቶች አንዱ እንዲሆን ረድቷል። የሚያሳዝነው ነገር ፣ የፋሲሊቲው ግንባታ ከዚህ ጉልህ እድገት ጋር እኩል መጓዝ አለመቻሉ ነው። ብዙ ትምህርት ቤቶች ካላቸው አቅም በላይ የሚሰጡት አገልግሎት፣ ከእኩልነትና ሚዛናዊነት እንዲሁም የጥራት ሁኔታዎች ጋር ተዳምሮ የትምህርት ቦርድ ወቅታዊውን የትምህርት ቤት ወሰኖች ግምገማ እንዲያካሂድ ትኩረት እንዲስብ አድርጓል። ይኼውም፦ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለመማር፣ ስለግንኙነቶች፣ ስለአክብሮት፣ እንዲሁም እኩልነትን ማንጸባረቅ የመሣሰሉ ዋነኛ እሴቶቹን የሚደግፍ ከፍተኛ ጥራት ያለው የትምህርት ፋሲሊቲ መስጠት መቻሉን  በቀጣይነት ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ ነው።

እስከ ዛሬ ምን ተከናወነ?
የኮቪድ-19 ቀውስ ከመከሰቱ በፊት እኛ ምዕራፍ I ስለ ተሳትፎ-ስምሪት ሂደት እና  ትንተና ጨርሰን ነበር። ይህም በመጋቢት 2020 ጊዜያዊ ሪፖርት በማቅረብ ተጠናቋል።
የምዕራፍ I ተሳትፎ ያካተተው፦

  • የትምህርት ቦርድ የህዝብ አስተያየቶችን የሚያዳምጥበት ጊዜ – ኖቬምበር 2019
  • በካውንቲው በጠቅላላ የሪጅናል ስብሰባዎች የተካሄዱበት ወቅት ከዲሴምበር 2019 - ጃኑወሪ 2020
    • ጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት - Gaithersburg High School
    • ጁሊየስ ዌስት መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት - Julius West Middle School
    • ዋይት ኦክ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት - White Oak Middle School
    • ዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት  - Walter Johnson High School
    • ሞንትጎሞሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት - Montgomery Blair High School
    • ኖርዝዌስት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት  - Northwest High School
  • ለመድረስ አስቸጋሪነት ካላቸው 12 ኢላማ ከሚደረግባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እና ሌሎችም ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረጉ የውይይት ክፍለጊዜዎች (ጃኑወሪ-ማርች 2019)

የምዕራፍ II ቀጣይ የመሳተፊያ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
የአማካሪ ቡድን "WXY Studio" ስቱዲዮ ለነዋሪዎች እና ለባለድርሻ አካላት ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች በኮምፒውተር እና በተጠቃሚዎች መካከል የመረጃ ልውውጥ በማድረግ በጥልቀት ጥናት እንዲያደርጉ የሚረዳ መተግበሪያ (ኤክስፕሎረር) እየሰራ ነው። ይህ መተግበሪያ ከእያንዳንዱ ትምህርት ቤት እስከ ዲስትሪክት ያሉት ተሳታፊዎች ሦስቱን ሌንሶች ማለትም፦ አጠቃቀም፣ የብዝሃነት ልዩነት፣ እና ቅርበት ያላቸውን ነገሮች እንዲረዱ ያስችላቸዋል፤ በሌላ በኩል ደግሞ እርስ በርሳቸው ተቀራርበው በሚገኙ ዲስትሪክቶች መካከል ያለውን ግንኙነት በጥልቀት እንዲመረምሩ ያስችላቸዋል።
ምዕራፍ II ማለት የተቻለውን ያህል በካውንቲ ውስጥ ነዋሪዎችንና ባለድርሻ አካላትን የእርስበርስ አሳታፊ መገልገያ በመጠቀምና በማሳተፍ ቁልፍ በሆኑ ጥያቄዎች ዙሪያ ያተኮረ ግብረመልስ ግብአቶችን በማግኘት ላይ ያተኮረ ነው።

  • በእርስዎ ትምህርት ቤት እና በአቅራቢያ ባሉ ትምህርት ቤቶች መካከል በአጠቃቀም፣ በብዝሃነት ልዩነት፣ እና ቅርበትን በተመለከተ ያለው ልዩነት ምን ያህል የተመጣጠነ ይመስልዎታል?
  • በካውንቲው ውስጥ ከትምህርት ቤት ወሰን ጋር በተያያዘ ከፍተኛ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የሚስተዋሉባቸው ቦታዎች/የመኖሪያ አካባቢዎች አሉ? ከሆነስ፣ ዬት እና ምን ዓይነት ተፈታታኝ ሁኔታዎች አሉ?
  • ትምህርት ቤቶችን በማካለል ረገድ፣ በየትኛው የትምህርት ቤት ደረጃ (የአንደኛ፣ የመካከለኛ፣ የሁለተኛ ደረጃ) ከፍተኛ አዳጋች ሁኔታ ያለባቸው ይመስልሃ(ሻ)ል? ምን ዓይነት ከባድ ወይም ተፈታታኝ ሁኔታዎች አሉ?
  • የትምህርት ቤት ክልል ከማበጀት ጋር በተያያዘ በጣም ከባድ፣ አዳጋች፣ ወይም ተፈታታኝ ሁኔታ ያላቸው የትኞቹ ትምህርት ቤቶች ወይም ቡድኖች ናቸው? ምን ዓይነት ከባድ ወይም ተፈታታኝ ሁኔታዎች አሉ?
  • አጠቃቀምን፣ የተለያ ብዝሃነትን ያቀፈ፣ እና ቅርበትን በሚዛናዊነት የማስጠበቅ እድል የሚታይባችው ትምህርት ቤቶች ፣ ከለስተሮች ወይም የካውንቲ ክፍሎች አሉ? የት እና እንዴት?

በዚህ ሂደት ውስጥ ቡድኑ፣ ህዝቡ ከትምህርት ቤት ወሰኖች ጋር በተያያዘ ቅድሚያ ስለሚሰጣቸው ነገሮች እንዲሁም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት እንዴት እንደተለወጠ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ይሰበስባል።
ሁለተኛው ዙር ቨርቹወል ተሳትፎ-ስምሪት የሚካሄደው በ2020 ፎል ላይ ሲሆን፥ የሚያካትተው፦

  • ህዝባዊ ስብሰባዎች
    • ሁለት በበይነመረብ የሚካሄዱ የማህበረሰብ ውይይቶች፦  እነዚህ ሁነቶች ስለተቀናጀ አሳታፊ መሣሪያ የተሟላ ማብራሪያ የሚሰጡ ከመሆኑም ሌላ ተሳታፊዎቹ መጀመሪያ ላይ ስለአጠቃቀሙ እንዲያጠኑ ያስችላቸዋል። መገኘት ለማይችሉ ሰዎች "webinars" በ MCPS ድረገጽ ላይ ይገኛሉ።
    • አሳታፊ የማህበረሰብ ግብረመልስ ግምገማ ክፍለጊዜ: ይህም ተሳታፊዎቹ በተለመዱት ውይይቶች ውስጥ ያለውን የግንኙነት መተግበሪያ በመዳሰስ እና ግብረመልስ በማጋራት ግኝቶችን በየጊዜው እንዲለዋወጡ ያስችላቸዋል።
  • የትምህርት ቤት ማህበረሰብ ተሳትፎ
    • የርእሰመምህር() ተሳትፎ፦ ቡድኑ የቅንጅት ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ርእሰመምህራን እና ረዳት ርእሰመምህራንን የሚያሳትፍ ከመሆኑም በላይ ከአስተማሪዎቻቸው፣ ከሠራተኞቻቸው፣ እና ከተማሪዎቻቸው ጋር በመናበብ ተግባብተው እንዲሠሩ ያስችላቸዋል።
    • የተማሪ ተሳትፎ፦ ቡድኑ ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በኮምፒውተር እና በተጠቃሚዎች መካከል ያለማቋረጥ የመረጃ ልውውጥ ማድረግ የሚያችላቸውን መሣሪያ በመጠቀም መልመጃዎችን ያዘጋጃል። ለአስተማሪዎች እና ለርእሰመምህራን በይነመረብ ላይ በኮምፒውተር እና በተጠቃሚዎች መካከል የመረጃ ልውውጥን ከቨርቹወል ትምህርት ጋር የማቀናጀት እና ከተማሪ ጋር በተናጠል ስለሚደረግ ቨርቹወል ክፍለጊዜ ቨርቹወል የስልጠና ክፍለጊዜ ይኖራል።

 

  • ኢላማ ያደረገ ተሳትፎ
    • አነስተኛ ቡድን ላይ ኢላማ ያደረጉ ስብሰባዎች፦ እነዚህ ስብሰባዎች የሚካሄዱት ለመገኘት ባለመቻል፣ በመጓጓዣ እጦት፣ በቋንቋና በመማር ችግሮች ወይም በሌሎች መሰናክሎች ምክንያት በማኅበረሰብ አቀፍ የተሳትፎ ሂደቶች ላይ ከማይካፈሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ነው።
  • ኦንላይን የሚካሄድ ዳሰሳ

ከላይ በተገለጹት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉ  በመረጃ ልውውጥ አሳታፊ መሣሪያ ድረ-ገጽ ላይ በኦንላይን የሚካሄድ ዳሰሳ እንዲሞሉ ይበረታታሉ። ይህ የዳሰሳ ጥናት ግኝቶችን ለመሰብሰብና ለትምህርት ቦርድ (BOE) ሪፖርት ለማድረግ እንደ ዋነኛ የአሠራር ስልት ያገለግላል።

ውጤቱ እንዴት በሥራ ላይ ይውላል?
የአማካሪው ቡድን አጠናቅሮ የሚያቀርበው ግብረመልስ በማጠቃለያ ሪፖርቱ ላይ ተካቶ ወደፊት በትምህርት ቤት ወሰኖች ላይ ዕቅድ አውጥቶ ለመነጋገር ለትምህርት ቦርድ ይቀርባል። ይህ ሪፖርት ሲጠናቀቅ ለቦርድ አባላት ወሳኝ የመረጃ ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል ከመሆኑም በላይ በማስረጃ የተደገፈ መረጃ እና በማህበረሰብ ግብረመልስ አማካኝነት ዲስትሪክት አቀፍ ጉዳዮችን ግንዛቤ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። የማጠቃለያው ሪፖርት በወሰን ለውጦች ላይ ምንም አይነት የውሳኔ ሀሳብ አይኖረውም።


ዓላማ

ዲስትሪክት አቀፍ ክልላዊ ትንተና ስለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ክልል ስለ ትምህርት ቤት የፋሲሊቲ አጠቃቀም፣ ስለተማሪዎች ስብጥር/student demographics፣ የትምህርት ቤት ምደባ እና የመጓጓዣ ፍሰት የመሣሰሉትን በርካታ ጭብጦችንና የማስረጃ ትንታኔዎችን አጠቃላይ ዳሰሳ ለመስጠት ዲዛይን የተደረገ ውጥን ነው። ጥናቱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከስፕሪንግ 2019 ጀምሮ ተሳትፎ በሚደረግበት ጥረት እና ሁሉንም አይነት የማህበረሰብ አባላትን በተለያዩ የውይይት መድረኮች በማሳተፍ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ይበልጥ ትርጉም ያላቸው በስብጥር፣ የተዋሃዱ እና ፈጣን ምላሽ ያላቸው ትምህርት ቤቶችን ለመፍጠር በሚደረጉ ጥረቶች በሂደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ውጣውረዶች/አዳጋች ነገሮችን ምኅዳር ሙሉ በሙሉ በመረዳት ላይ የሚገነባ ነው።

ለምን አሁን ይደረጋል?

ባለፉት ሃያ ዓመታት፣ ወደ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከ30,000 በላይ ጨምሯል። ይህ እድገት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በአገር አቀፍ ደረጃ ብዝሃነት ካላቸው ከከፍተኛዎቹ አንዱ እንዲሆን ረድቷል። ያለመታደል ሆኖ፣ የፋሲሊቲ ግንባታው ይህንን ከፍተኛ እድገት በሚመጥን ደረጃ አልሆነም። ከአቅማቸው በላይ የተሸከሙ የበርካታ ትምህርት ቤቶች ሁኔታ፣ በእኛ የሚዛናዊነት እና የላቀ ችሎታ ዘላቂ ትኩረት ጋር ተዳምሮ፣ MCPS ስለ ትምህርት፣ ግንኙነት፣ መከባበር፣ በትምህርት ምጡቅነት፣ እና ሚዛናዊነትን የመሣሰሉ የ MCPS ዋና እሴቶችን ለማጎልበት የሚያስችሉ ከፍተኛ-ጥራት ያላቸው ፋሲሊቲዎችን ለመስጠት የትምህርት ቦርድ የወቅቱን የትምህርት ቤት ክልሎችን ዳሰሳ እንዲያካሄድ/ጥናት እዲያደርግ አነሳስቷል።

ጠቃሚ ማስታወሻ፦

ይህ ጥናት ውጤታማ የሚሆነው የዳሰሳ ዝርዝር ትንታኔ እና የማህበረሰብ ተሳትፎ ሂደትን አጠቃሎ በማቅረብ ይሆናል። የክልል ክለሳ መደረግ ያለባቸውን አስተያየቶች/ሪኮመንዴሽን አያደርግም።

ስለማካለል ትንታኔ የኢ-ሜይል ምዝገባ

ስለ ትምህርት ቤት የክልል ትንታኔ እና ተሳትፎ ጋር የሚገናኙ ተግባሮችን ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት የእርስዎን ኢ-ሜይል አድራሻ ይስጡ። ኢ-ሜይል

Register for the webinars and virtual community session

Phase II Engagement Flyer

ቀጥሎስ ምን ይደረጋል?

የመጀመሪያ ደረጃ/Phase 1፦ ፎል እና ዊንተር (2019)

  •  
    የመረጃ ትንተና

    ከሌሎች የትምህርት ዲስትሪክቶች ሁኔታ ጋር ለማገናዘብ ጭብጦችን/ማስረጃዎችን እና የጥናት ግኝቶችን ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጋር የማነፀጸሪያ ወለል

    በአካባቢ ሁኔታ ላይ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ቤት ክልሎችን ወቅታዊ ሁኔታዎች ትንታኔ በመስጠት በተሟላ ሁኔታ መረዳት

    ከጭብጥ-የመረጃ ትንታኔ እና በማህበረሰብ ተሳትፎ እንቅስቃሴዎች የተረጋገጠ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ውጤታማነት-ስኬታማነት መለኪያዎችን ለይቶ ማወቅ

    በእድሎች እና በማካካስ መካከል ቁልፍ ሚናዎችን ለመመርመር የሚያስችሉ እርስ በርስ አሳታፊ የብቃት/የቅልጥፍና tools/መሣሪያዎችን ማዳበር

  •  
    የተሳትፎ ተግባሮች፦ የማህበረሰብ ግንዛቤ እና መረጃ ማሰባሰብ

    የተሳትፎ እንቅስቃሴዎቹ ዒላማ የሚያደርጉት አሁን በሥራ ላይ የሚገኙት የወሰን ክልሎች ያላቸውን ቁልፍ እድሎችን እና አዳጋች ሁኔታዎችን ለካውንቲው ነዋሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጥ እና የውይይት መድረክ መፍጠር ነው።

  •  
    ሌላ የመድረስ እንቅስቃሴ ኖቬምበር አጋማሽ ላይ ይጀመራል

    የትምህርት ቦርድ ህዝባዊ ውይይት-ሸንጎ (ኖቬምበር 18/2019 850 Hungerford Dr. Rockville, MD)

    በካውንቲው ውስጥ በርካታ የሪጅናል ስብሰባዎች የሚካሄዱባቸው (ቀኖች እና ቦታዎች ቶሎ ይገለጻሉ)

    የህዝባዊ ስብሰባዎች ተግባሮች (ቀኖች እና ቦታዎች ቶሎ ይገለጻሉ)

    ለመድረስ አዳጋች የሆኑ ማህበረሰቦችን እና ሌሎች ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ላይ ያተኮረ የመድረስ አገልግሎት - Outreach/Engagement

Phase/ምዕራፍ 2፦ ዊንተር እና ስፕሪንግ (2020)

  •  
    የመረጃ ትንተና
     

    የመረጃ ትንታኔው ካለፈው ትንታኔ በመነሣት ያሉትን እድሎች እና የማቻቻል ሁኔታዎችን በመፈተሽ የእርስበርስ ግንኙነት ለማዳበር የሚያስችል መገልገያ/tool በመፍጠር የፋሲሊቲ አጠቃቀም፣ ስለተማሪዎች ስብጥር/student demographics፣ እና የመጓጓዣ ፍሰት የመሣሰሉት ትንታኔዎች ላይ ያተኩራል።

  •  
    ሃሳቦችን እና መመዘኛዎችን መፈተሽ
     

    ሃሳቦችን እና መመዘኛዎችን መፈተሽ/ቴስት ማድረግ የሚያተኩረው ከመጀመሪያው ምዕራፍ/Phase 1 የተገኙ መረጃዎችን/ዳታዎችን የተሳትፎ ግኝቶችን በስኬት መመዘኛዎች መካከል ያሉትን እድሎችና ማካካስን በማገናዘብ የርስበርስ ግኝቶችን መሳሪያ/interactive tool መረጃ/ዳታ የማቅረብ ሂደት ይሆናል።

  •  
    የመድረስ እንቅስቃሴ ዊንተር 2020 ይጀመራል
     

    በካውንቲው ውስጥ በርካታ የሪጅናል ስብሰባዎች የሚካሄዱባቸው (ቀኖች እና ቦታዎች ቶሎ ይገለጻሉ)

    ለመድረስ አዳጋች የሆኑ ማህበረሰቦችን እና ሌሎች ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ላይ ያተኮረ የመድረስ አገልግሎት - Outreach/Engagement

የጊዜ ሠሌዳ-ገደብ

timeline

ምዕራፍ 2 የጊዜ ሠንጠረዥ

Boundary Analysis Timeline Phase II - Amharic

የትኩረት አቅጣጫዎች

አሁን ያሉትን የትምህርት ቤቶች ክልላዊ-ወሰን አገላለጽን አጠቃላይ ሁኔታ ለመረዳት/comprehensive understanding የሚከተሉት ሁኔታዎች ይተገበራሉ። እነዚህ የትኩረት ነጥቦች በተሳትፎ ሂደት የሚጣሩ ሲሆን ቀጥሎ ያሉትን ያካትታሉ፦

equity
ፍትኃዊነት/ሚዛናዊነት፦:
  • የተማሪዎች ስብጥር / Demographics
  • የማህበራዊ-ኢኮኖሚ ሚዛናዊነት
capacity
አቅም፦
  • የፋሲሊቲ አጠቃቀም እና አቅም
  • የትምህርት ቤቶች አወቃቀር እና የመጋቢ ት/ቤቶች አመዳደብ ቅጥ
  • የተረጋጋ የትምህርት ቤት ምደባ
bus
ተደራሽነት፦:
  • የትምህርት ቤቶች መልክአምድራዊ አጎራባችነት
  • በሥራ ላይ ያለው የትምህርት ቤት አውቶቡስ መጓጓዣ አሠራር

መሠረታዊ መርኆች

College info

1 የመረጃ ትንታኔ

  • ትንታኔዎችን ከሁኔታዎች ጋር ማገናዘብ በተሳትፎ እንቅስቃሴ ወቅት በሙሉ ለተነሱ ጉዳች
  • የመረጃ እና የጥናት አድልዎ ማስወገድ የጥናት ግኝቶችን ከሌሎች አግባብነት ካላቸው የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች ጋር በማወዳደር
  • አጠቃለው የሚይዙ ሞዴሎችን/ናሙናዎችን መፍጠር ቁልፍ በሆኑ የተግባር አመላካቾች መካከል ያሉትን እድሎች እና የማቻቻል/የማካካስ ሁኔታዎችን የሚፈትሹ
community icon

2 የማህበረሰብ ተሳታፊነት

  • በፈጠራ የሚደረጉ ግንኙነቶችን እና ሌሎችን የመድረስ ስትራቴጂዎችን መጠቀም በካውንቲው ከሁሉም አቅጣጫ ተሳትፎን ለማሳደግ
  • በሁሉም የተሳትፎ እንቅስቃሴዎች አካታች የሆኑ አካባቢዎችን ማጎልበት/ማሳደግ/ማበረታታት ከተለያየ ዘር፣ ጎሣ፣ ባህል እና ኤኮኖሚያዊ ሁኔታ ብዝሃነት ያላቸው ሰዎች ሁሉ ምቾት እንደሚሰማቸው ማረጋገጥ
  • ተሳትፎን ማበረታታት-ማደፋፈር አውደጥናቶችን በመሣሰሉ በጥንቃቄ የተዘጋጁ መርሃግብሮች አማካይነት
  • በጥልቀት የተጠኑ የጥናት ውጤትቶችንና-ግኝቶችን ማካፈል የዳታ/መረጃ ትንታኔዎችን ይፋ-ግልጽ በሚያደርጉ በተለያዩ መተላለፊያ መንገዶች አማካይነት ከተሳትፎ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተጨባጭ የሆኑ ውጤቶችን ማረጋገጥ
  • ግብረመልስ የሚሰጥበት ቀለበት-ቀዳዳ መፍጠር በርካታ የአውታረ-መረብ የዳሰሳ መተግበሪያዎችን በመጠቀም